በኮልፌ ክ/ከተማ አስተዳደር በየጊዜው እየተካሄዱ ያሉት የተገልጋይ አገልጋይ የፊት ለፊት እንጠያየቅ መድረክ የህበረተሰቡን ተሳትፎ በማረጋገጥ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በመመለስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ።
በዛሬው እለት የተካሄደው 3ኛው ዙር የእንጠያየቅ መድረክ የክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት፣ የኮሙኒኬሽንና የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤቶች በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች በተገኙበት ተካሄዷል ፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወልደሚካኤል ባደረጉት ንግግር አስተዳደሩ ፈጣንና ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት የነዋሪውን ህይወት ለማሻሻል በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ገልፀው መሰል የፊት ለፊት መድረኮችም አዳጊ የሆነውን የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘውዱ ከበደ እንደተናገሩት በከተማው ብሎም በክፍለ ከተማው ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸው የገለፁ ሲሆን የተሰሩ ስራዎችን ለማላቅ እና በሂደቱ የሚያጋጥሙ ጉድለቶችን ለማረም መሰል የእንጠያየቅ መድረክ ከተገልጋዪና አገልጋዪ ጋር በማዘጋጀት ተቀራርቦና ተባብሮ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ምርምር ሀይሌ በበኩላቸው አስተዳደሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳጊ ውጤቶች እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀው እነዚህን የበለጠ ለማስፋት ከተገልጋዪ ማህበረሰብ ተቀራርቦ መስራት አስፋለጊ በመሆኑ መሰል መድረኮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የሚመለከታቸው የተመረጡ የፅ/ቤት ሀላፊዎችም በተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.