"ክብርት ከንቲባችን የእኛን ህይወት እንደታደጉት ሁሉ እኛም ከራስ አልፈን የሌሎችን ህይወት ለመታደግ በቅተናል፡፡"
ከነገዋ ማዕከል ተመርቀዉ በስራ ላይ የተሠማሩ ሴት እህቶች
ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በተለያዩ ምክንያቶች ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራት ተጋላጭ የሆኑ ሴት እህቶቻንን አማራጭ የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ መሰማራት እንዲችሉ ብቁ የሚያደርጋቸዉን የስነ-ምግባር፤የስራ ባህል እና የስራ ስምሪት እንዲፈጠርላቸዉ የተገነባ ባለፈርጀ ብዙ ማዕከል መሆኑን በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ከንቲባዋ ልማት የሰዉን ህይወት የማይቀይር እና ለሰዉ ተስፋ የማይሰጥ ከሆነ ብቻዉን መሰረት ልማት ሰርተን ሃገር ብሎም ከተማ ለዉጠናል የሚል መለኪያ የሌለን በመሆኑ በብልፅግና ጉዞ መለኪያችን የሰዉን ህይወት ከመቀየር ጋር የተቆራኘ ነዉ ማለታቸዉም ይታወሳል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ይህን እዉን ለማድረግ ከ1ኛ እስከ 3ኛዙር በተለያየ የሙያ መስኮች ከማዕከሉ ሰልጥነዉ ለወጡት ተመራቂዎች የስራ እድል በመፍጠር ሁለተናዊ ተጠቃሚነታቸዉን ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በማዕከሉ በ4ኛዉ ዙር ከ1ሺ ያላነሱ ሴት ሰልጣኞች እየሰለጠኑ ይገኛሉ፡፡
በተለያዩ የሙያ መስኮች ሰልጥነዉ ወደ ስራ የተሰማሩ ሴት እህቶቻችን እንደተናገሩት በተፈጠረልን ልዩ እድል ከከባድና አስከፊ ከነበረዉ ህይወታችን ተላቀን ባገኘነዉ ልምድና በቀሰምነዉ እዉቀት የነገዉ ህይወታችን ብሩህ የሚሆንበት ሁኔታ መፍጠር ችለናል ብለዋል፡፡
አክለዉም በማዕከሉ በተፈጠረላቸዉ የስራ እድል መሰል ሴት እህቶቻቸዉን እያሰለጠኑ እንደሚገኙ እና በከተማዋ ባሉ የመንግስት ተቋማት ሳይቀር እየተገኙ ስልጠና የሚሰጡ መኖራቸዉንም በማብራሪያቸዉ ገልፀዋል፡፡
በወሰዱት ልዩ ልዩ የስራ ስምሪትም ለሌሎችም የስራ እድል በመፍጠር ህይወታቸዉን ለመታደግ መብቃታቸዉን ገልፀዉ በዉጪ ሃገርም በተዘረጋዉ የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
ይህም ሌሎች የእኛን ህይወት እንደታደጉት ሁሉ እኛም ከራስ አልፈን የሌሎችን ህይወት ለመታደግ የበቃንበት የከተማ አስተዳደሩ ፍሬ ማሳያ ነዉ ሲሉ በስራ ላይ የተሠማሩ ሴት እህቶች ገልፀ::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.