አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የኪነ-ጥበብ ማዕከል ለማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ፥ የአፍሪካ የኪነ-ጥበብ ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እና በተግባር እያሳየች ያለች ከተማ!

አዲስ አበባ፥ የበርካታ ከያኒያን መፍለቂያ ከተማ ብትሆንም፣ ሙያተኞችን እና ታዳሚውን የሚመጥን የጥበብ መከወኛ እና መመልካቻ፣ መታደሚያ እና ማሰብያ ስፍራ እምብዛም  አልነበራትም። 

ከለውጡ በፊት  የነበሩ ቴአትር ቤቶች  እና ሲኒማ ቤቶች እርጅና የተጫናቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ የጥበብ ቤተሰቦችን የማይመጥኑ ነበሩ።

አሁን፥ ከለውጡ በኃላ፣ በተከናወነው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራ፣ በተለይም በከተማዋ በሚከናወኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እኩል ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት  በርካታ አንፊ-ቴአትር  ስፍራዎች፣ ፕላዛዎች  እና ምቹ የማሰብያ ፓርኮችን መገንባት ተችሏል ።

በሃገራችን የኪነጥበብ ታሪክ በልዩነት የሚጠቀሰው፣ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የዘመኑ ቴክኖሎጂ የታጠቀው የወጣቶች እና ህፃናት ቴአትር ኮምፕሌክስ፤ እንዲሁም፣ ግዙፉ የሲኒማ ኮምፕሌክስ በቅርቡ ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉ የኪነጥበብ ማዕከልነቷ ማረጋገጫ ምስክሮች ናቸው።

ከተማ አስተዳደሩ ልማት ሁሉን አቀፍ መሆኑን በመገንዘብ፣ አሁንም በሚሰራቸው የልማት ስራዎች ሁሉን አካታችነት ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.