በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ኮልፌ የገበያ ማዕከል ኤግዚብሽንና ባዛር በዛሬው እለት በይፍ ተከፍቷል።
ኤግዚብሽንና ባዛሩን በይፍ የከፍቱት የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኋላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለፁት የከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ከነዚህ ስራዎች ውስጥም የገበያ ማዕከላትን በማስፋፋት አምራችና ሸማችን በቀጥታ በማገናኘት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማቅረብ መቻሉን አስገንዝበዋል ።
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል እንደተናገሩት የኤግዚቢሽን እና የባዛሩ መከፈት ዋና ዓላማ ለገበያ ማዕከሉ አስፈላጊውን መሰረተ ልማት እና የምርት አቅርቦትን ባጭር ጊዜ ውስጥ በሟሟላት በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ በማስገባት ለህብረተሰቡ ተገቢውን የምርት አገልግሎት በመስጠት ኑሮ ውድነት ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል ።
በኤግዝብሽኑ እና ባዛሩ የግብርና የሰብል ምርቶች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ኢንደስትሪ ምራቾችች፣ ባህላዊ አልባሳት ፣ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም ሌሎች መሰል ምርቶች እንደሚቀርቡ ተገልፃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.