ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በልደታ ክፍለ ከተማ 106 የቀበሌ ቤቶችን ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው አቅመ ደካሞች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአገር ባለውለታዎች ለሆኑ እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ የከተማችን ነዋሪዎችን ለይተን በእጣ አስተላልፈናል ።

ከህዝብ ጋር ባደረግነው ውይይት የተሰጡንን ጥቆማዎችን ጭምር  ተጠቅመን ባደረግነው ማጣራት የለየናቸውን  ነዋሪዎቻችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፣ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የተዘነጉ፣ ጧሪና ደጋፊ  የሌላቸውን አቅመ ደካማ ወገኖችን እንባ በማበስ እና ከነበሩበት አስከፊ ሕይወት በመታደግ ነገን በተስፋ እንዲያዩ የሚያስችል ስራ ተከናውኗል ።

በተለይም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ከቁርጡሚ ወንዝ ዳርቻ ለተነሳችሁ፣ በሶስተኛ ወገን ክርክር ምክንያት  ስትንገላቱ የቆያችሁ  ዛሬ ችግሩን ፈተን የመኖሪ የቤት ስላገኛችሁ  እጅግ ደስተኞች ነን፤  እንኳን ደስ አላችሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.