በከተማችን እየተተገበሩ ካሉ የዜሮ ግብ ፕሮጀክቶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በከተማችን እየተተገበሩ ካሉ የዜሮ ግብ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ተረጂነት እና ልመናን ዜሮ ማድረግ ነው።

ዛሬ ማለዳ በአዲስ ከተማ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በየካ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች፣ አራት G+4 የማምረቻ እና መሸጫ ህንፃዎችን ከዚህ ቀደም በምግብ ዋስትና (ሴፍቲኔት) ፕሮግራም ታቅፈው ሲሰሩ  ለነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች አስረክበናል።

የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች  976   አንቀሳቃሾች ሲሆኑ፣ በ292 ኢንተርፕራይዞች እንዲደራጁ ተደርጓል።
የከተማ አስተዳደራችን በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በማምረቻና መሸጫ ቦታ አቅርቦት፣ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ህይወት በመለወጥና ከድህነት በማውጣት ኑሯቸውን በዘላቂነት ለመምራት እንዲችሉ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።

አስተዳደራችን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ520 ሺህ በላይ  የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን በተለያዩ ዘርፎች የስራ ዕድል በመፍጠር ከተረጂነት ወደ አምራችነት ማሸጋገር ችሏል።
ውድ ተጠቃሚዎች፣ የተፈጠረላችሁን የስራ ዕድል በአግባቡ  በመጠቀም ከተረጂነት ወደ አምራችነት በመሸጋገር በአጭር ጊዜ ውጤታማ ሆናችሁ ስላየን እጅግ ደስተኞች ነን።

ዛሬ ያስረከብናችሁ የመስሪያ ቦታ ነገ የእናንተ እህቶች፣ ወደፊትም ወንድሞችና ልጆች ተረክበው የሚሰሩበት መሆኑን ተገንዝባችሁ በኃላፊነት ልትጠቀሙበት ይገባል።
በቀጣይም በስልጠና ያገኛችሁትን ክህሎት በስራ ህይወታችሁ   በመተግበር በርትታችሁ የበለጠ ውጤታማ በመሆን ሌሎችም የእናንተን መንገድ እንዲከተሉ ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.