"በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት፤ለሃገር ልማት በማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት፤ለሃገር ልማት በማዋል በኩል ረጅም መንገድ መጓዝ ችለናል፡፡"ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በዛሬዉ እለት 22ኛዉ ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ከተማ አቀፍ ንቅናቄ የማጠቃለያ መደረክ አድዋ በሚገኘዉ ፓንአፍሪካ አዳራሽ  ተካሔዷል።

"ትዉልድን በስነ-ምግባር፤ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ሃሳብ በተለያየ ደረጃ እና በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር መቆየቱና የዛሬዉም ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ መድረክ መሆኑ ታዉቋል፡፡

በክብር እንግድነት ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት ሙስና ፀያፍ የሆነ፤የሃገርን ገፅታ የሚገታ፤ትዉልድን የሚጎዳ እና ኢ-ፍትሃዊነትን የሚያነግስ ተግባር በመሆኑ የመላዉ ማህበረሰብን እና የሁሉንም ተቋማት ትግል የሚጠይቅ ቀዳሚ ጉዳይ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ መንግስት በወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም ፤በተሰራዉ ስራ እና በተፈጠሩ አስቻይ ሁኔታዎች ሙስናን በመከላከል በእርግጠኝነት የሃገር ሃብት ለሃገር ልማት በማዋል በኩል ረጅም መንገድ መጓዝ ችለናል ብለዋል፡፡፡

በዚህም በየዘመናቱ በነበሩ የየስርዓቱ መሪዎች የሃገር ሃብት ወደ ዉጪ በማሸሽና በማከማቸት፤  ከባለሃብቶች ጋር ከሃገር ዉጪ በመስራት የሃገራችንን ልማት እና እድገት የሚያቀጭጭ ተግባር በዚህ ዘመን ታሪክ ሆኖ አልፏል ብለዋል፡፤

ይህን ጅምር ስራ የበለጠ ለማጠናከር በእያንዳንዱ ስራችን ሙስናን የሚፀየፍ ትዉልድ በማፍራት ረገድ ትላልቅ ሃላፊነት ያለብን ተቋማት አቅደን መስራት እና ለዉጥ ማምጣት ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል፡

አክለዉም ሁልጊዜ በምንሰራዉ ስራ ሙስና እንዳይተገበር መከላከል ብቻ ሳይሆን ሙስናን  የሚፀየፍ ትዉልድ መገንባት ላይ ስለመሆናችን ራሳችንን መጠየቅ እና ከምንናገረዉ ባሻገር የምንናገረዉን ሁነን መገኘት ትዉልድ እንዲከተለን የሚያደርግ እዉነታ ስለሆነ ይህን መርህ በጥብቅ ልንተገብረዉ ይገባል ብለዋል ከንትባዋ፡፡

መላዉ አመራር በፀረ-ሙስና ትግሉ ላይ የሃሳብና የተግባር አንድነቱን በማፅናት በግለሰቦች ደረጃ ሳይቀር በመንግስት ኃላፊዎችና በሠራተኞች የሚታዩ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮች ላይ ሁላችንም እጅለ ለእጅ ተያይዘን መስራት እና  ትዉልድ ላይ የሞራል ልእልና እንዲበለፅግ ስር የሰደደዉን ኢፍትሃዊ አካሄዶችን መዋጋት ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል፡፤

በመጨረሻም ዛሬ ያገኘነዉን ዉጤት ለማወደስ ሳይሆን የበለጠ የፀረሙስና ትግሉን በማጠናከር ተጠያቂነትን ለማስፈን ቃል የምንገባበትና የገባነዉን ቃል የምናድስበት ስለሆነ ሃላፊነታችንን በአግባቡ በመወጣት፤አሰራራችንን ግልፅ በማድረግ ፤ከሰዉ ንኪኪ ነፃ ሆነን ህዝባችንን እናገልግል በማለት መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ በከተማዋ በተደረገዉ  የፀረ-ሙስና ትግል ላይ  የላቀ አስተዋፅአ ላበረከቱ ተቋማት እውቅና ተሰጧል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.