“ዛሬ በልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ዛሬ በልደታ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተመረቁት ስማርት ወረዳ ህንፃዎች “

የልደታ ክፍለከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ሕንፃ 
👉 12,000 ካ.ሜ አጠቃላይ የወለል ስፋት አልው ፣ 
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 01 
👉7,260 ካ.ሜ አጠቃላይ የወለል ስፋት አለው
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 12  
👉8,122 ካ.ሜ አጠቃላይ የወለል ስፋት አለው 

እነዚህ ዘመናዊ የአስተዳደር ሕንፃዎች እያንዳንዳቸው 
👉ከ60 በላይ ቢሮዎችና ተጨማሪ የስራ ስፍራዎች አሏቸዉ ፣
👉  ስማርት ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸውና የአካል ጉዳት ያለባቸውን ወገኖች ከግምት ያስገቡ ሊፍቶች አሏቸው፣
👉የህፃናት ማቆያ ፣ 
👉ጂምናዚየም ፣ 
👉የመጀመሪያ ሕክምና አገልግሎት መስጫ ፣
👉 400 መቀመጫዎችን መያዝ የሚችሉ መሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ 
👉ከምድር በታች እና በምድረ ግቢዎቹ የሚገኙ የተሸከርካሪ ማቆሚያዎች ፣ 
👉አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ-ልማቶች የተሟሉላቸው ናቸው፡፡
እነዚህ ዘመናዊ ሕንፃዎች ከዚህ ቀደም እንደምናውቃቸው የወረዳ አስተዳደር ሕንፃዎች አይነት ሳይሆኑ በቀጣይ  የሚሰጡ የስማርት (ስሉጥ) ከተማ አገልግሎቶችን ጭምር ታሳቢ ያደረጉ የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማቶችን ያሟሉ ናቸው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.