አዲሱ የተቀናጀ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ዲጂታል ስርአት (Civil Registration and Vital Statistics with e-ID) ምን አይነት አገልግሎቶችን ይሰጣል?
ባለጉዳዮች የሞባይል ስልካቸውን፣ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም በአካል ሳይገኙ ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል
የግዴታ ፎርም መሙላትን የሚያስቀር፣ በኢምግሬሽን፣ በጤና፣ በፍርድ ቤት፣ በብሄራዊ መታወቂያ እና በሎሎችም በተቋማት መካከል ቅንጅት እና መናበብን ይፈጥራል
የመታወቂያ አሰጣጥ ላይ ያለ ባለፋይሉ ባለቤት ይሁንታ ለማንም በእርሱ የቤት ቁጥር መታወቂያ እንዳይሰጥ መቆጣጠር የሚያስችል እና ሌሎችም በርካታ ዝርዝር አገልግሎቶችን አጣምሯል
ስራ ላይ የዋለው የ Civil Registration and Vital Statistics with ID ሲስተም ከዚህ ቀደም በወረቀት ይሰጡ የነበሩ የተለያዩ እንግልቶችን ያስቀራል
ብልሹ አሰራርን በመከላከል ግልጽነትን ያመጣል
ቴክኖሎጂዉ የበለጸገዉ በኢትዮዽያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ነዉ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.