አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም አቀፍ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ "አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

"አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት"

አካል ጉዳተኞች የትምህርት እድል፣ የጤና እንክብካቤ፣ የሥራ ዕድል፣ ማኅበራዊ ጥበቃ አለማግኘትን እንዲሁም በማኅበረሰቡ ዘንድ ከተንሰራፋው የተዘባ አመለካከት በሚመነጩ እንቅፋቶች ምክንያት የሚደርስ መድልዎን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን የአካል ጉዳተኞችን መብቶችና ደኅንነቶች የማስፋፋት ዓላማን አንግቦ በየዓመቱ ኅዳር 23 ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። በተመሳሳይ ቀኑ በአካል ጉዳተኞች መብቶች ዙሪያ እና ማኅበረሰቡ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አካል ጉዳተኞች ላይ የሚያደርሰውን መድሎ በተመለከት ግንዛቤ ለመፍጠር ዓላማ ይውላል።

በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች የትምህርት እድል፣ የጤና እንክብካቤ፣ የሥራ ዕድል፣ ማኅበራዊ ጥበቃ አለማግኘትን እንዲሁም በማኅበረሰቡ ዘንድ ከተንሰራፋው የተዘባ አመለካከት በሚመነጩ እንቅፋቶች ምክንያት የሚደርስ መድልዎን ጨምሮ በርካታ ተግዳሮቶች ይገጥሟቸዋል። መንግሥት ተደራሽነትን እና የአካል ጉዳተኞችን መካተት ለማረጋገጥ ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶችን በማስመዝገብ ቁርጠኝነት ማሳየትን ጨምሮ የሰብአዊ መብቶች መስፋፋት እና ጥበቃን በማረጋገጥ ረገድ ተቀዳሚ ኃላፊነት አለበት። ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ለአካል ጉዳተኞች መብቶች በመታገል እና በመወትወት መሪነታቸውን እና ቁርጠኝነታቸውን ማሳየት አለባቸው።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.