"ሀብትን በተገቢዉ መጠቀም ሀገርንና ትዉልድን ሲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ሀብትን በተገቢዉ መጠቀም ሀገርንና ትዉልድን ሲገነባ ሀብትን ያለአግባብ ማዋል ሀገርና ትዉልድን የሚያዳሽቅ የዓለም ነባራዊ እዉነታ ነዉ ።"የአዲስ አበባ ከተማ ም/አፈ-ጉባዔ ወ/ት ፋኢዛ መሀመድ

በዓለም ለ22ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ21ኛ ጊዜ በመከበር ላይ የሚገኘዉ የፀረ-ሙስና ቀን "ትዉልድን በመልካም ስነ_ምግባር ፤ተቋምን በአሠራር" በሚል መሪ ቃል  ዛሬ በፖናል ዉይይት ተከብሯል።

ፓናል ዉይይቱን  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ  የስነ_ምግባርና  ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጋራ  ያዘጋጁት  መሆኑ ታዉቋል

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ም/አፈ-ጉባዔ እና የእለቱ የክብር እንግዳ ወ/ት  ፋኢዛ መሀመድ ፓናል ዉይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ሀገራት የሚያድጉትና የሚበለፅጉት  በዉስጣቸዉ ያለዉን ሀብት በተገቢዉ ሲጠቀሙበት  መሆኑን እና  ሀብትን ላልተገባ መዋል ሀገርን  እና ትዉልድን  የሚያዳሽቅ የዓለም ነባራዊ እዉነታ ነዉ ብለዋል።

ለሀገር ልማትና እድገት ፀር ከሆኑት ከሌብነትና ብልሹ አሰራር  ለመታደግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና  ኮሚሽን በከተማችን  የፀረ ሙስና ትግሉን በማፋፋም ተጨባጭ ስራዎችን በመስራቱ በከተማ ብሎም በሀገር እድገት ላይ ትርጉም ያለዉ ለዉጥ እያመጣ ይገኛል ብለዋል።

አክለዉም በኮሚሽኑ ከተማችንን መሠረት ያደረጉ ከ 380 በላይ ጥናቶች  መደረጋቸዉን  ጠቁመዉ ሰፊ እና ወጥነት ያለዉ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ገንዘብና  መሬት ከስርቆትና ከምዝበራ የዳነበት እንዲሁም በዚህ እኩይ ተግባር የተገኙ ሠራተኞችን ጭምር ለህግ በማቅረብ ከ12ሺ በላይ የመግስት ሠራተኞች የተባረሩ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ የዛሬዉ ፓናል ዉይይትም ከተማዋ የጀመረችዉን የፀረ_ሙስና ትግል ይበልጥ ለማጠናከር  እና ሁሉም ለጋራ ልማትና እድገት  በጋራ በመቆም ሀገራዊ ግዲታዉን እንዲወጣ ያለመ በመሆኑ ትዉልድን በስነ ምግባር የማነፅና ተቋምን በአሰራር  የማጠናከር ስራ ላይ የበኩላችሁን ሚና  እንድትወጡ ሲሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.