በልደታ ክ/ከተማ የልማትና የመልካም አስተዳደር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በልደታ ክ/ከተማ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በላቀ ለመፈፀም የሚያችል የእንጠያየቅ መድረክ ተካሄደ

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት የተነሱ ጥያቄዎች መሬት ላይ ያሉ ናቸው ያለንን አቅም አሰባስበን ከጊዜ ጋር አስልተን በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ እቅድ እንፈታለን ብለው  ከአሁን በኃላ የሚከርም የመልካም አስተዳደር ችግር ስለማይኖር  በየደረጃው ካለ አመራር ጋር ተነጋግረን ክትትል አድርገን እየፈታን እንሄዳለን ሲሉ ገልፀዋል።

ፈጣን፣ መሬት የነካና እውነተኛ ለውጥ የሚኖረው የህዝብን ችግር አዳምጦ ለችግሩም የህዝብን አቅም በመጠቀም ፈጣን ምላሽ መስጠት ሲቻል ነው ያሉት ወ/ሮ ልዕልቲ በዚህም አገልግሎት አሰጣጣችን ፈጣንና ምላሽ ሰጭ እንዲሆን በትኩረት እየሰራን ነው በማለት ተናግረዋል።

የተገልጋይ እንግልት እና ምልልስ የሚበዛባቸውን ተቋማት ለይተን የማሻሻል ስራ እየሰራን ነው ያሉት ወ/ሮ ልዕልቲ በዚህም በቢሮ ከምንሰጣቸው ፈጣንና ግልፅ አገልግሎት በተጨማሪ ተገልጋይ ቢሮ ላይ መጥቶ ሳይነግረንም ጭምር ወርደን አይተን ችግር እየፈታን እንገኛለን በማለት ገልፀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደተናገሩት የህዝብን ፍላጎት መሰረት አድርገን የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን እያከናወን ነው ብለው በዚም 24/7 እየሰራን በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል ሲሉ ገልፀዋል።

ያለህዝብ ተሳትፎ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት አቶ አራርሳ በጋራ ተጋግዘን ችግሮችን እየፈታን ተጠቃሚነትን በላቀ ሁኔታ እናረጋግጣለን በማለት ገልፀዋል።

አቶ አራርሳ አክለውም ህዝብን የሚያማርሩ ችግር የሚፈጥሩ ለአገልግሎት ጉቦ የሚጠይቁ አካላት ካሉ በጋራ እያረምን ፍትሀዊነትን እናረጋግጣለን ሲሉ ገልፀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሲፈን ባዩ እንደተናገሩት ስንመካከር ስንነጋገር የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎቻችን የበለጠ ይሰምራሉ ብለው መነጋገርና ለገጠሙ ችግሮች በጋራ መስራት በክ/ከተማችን ባህል እየሆነ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የምናከናውናቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ መሰል የእንጠያየቅ መድረኮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ያሉት  ወ/ሮ ሲፈን የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤትም  መድረኮችን እያዘጋጀ ህዝብና መንግስትን ድልድይ ሆኖ የማገናኘት ስራ ያከናውናል ሲሉ ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.