“የአዲስ አበባን ልማትና እድገት ለመግለጥ ከኢቢሲ ጋር መስራት ወሳኝ ነው”፦ አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሔር
የአዲስ አበባን ልማትና እድገት ለመግለጥ ከኢቢሲ ጋር መስራት ወሳኝ ነው ስሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሔር ገለጹ።
በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ ለመስራት ውይይት አድርገዋል።
ኢቢሲ አንጋፋ እና በሀገራችን የሚዲያ ታሪክ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሚድያ መሆኑን ያነሱት አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሔር የአዲስ አበባን ልማትና እድገት ለማሳየት ከኢቢሲ ጋር መስራት ወሳኝ መሆኑን ነው የገለፁት።
ኢቢሲ የሀገረ መንግስቱን እሳቤዎችና ፍላጎቶች መሰረት አድርጎ ይሰራል ያሉት የኢትዮጵያ ብሮዲካስቲንግ ኮሮፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ በበኩላቸው በአዲስ አበባ ከተማ እየተሰሩ ያሉ የብልጽግና ምሳሌ የሆኑ የልማት ስራዎችን በማስታዋወቅ አብሮ መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ኢቢሲ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር፤ ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር፤ በገዥ ትርክት ግንባታ ላይ እንዲሁም ወንድማማችነትን እና አብሮነትን ለማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል አቶ ቢኒያም።
ኢቢሲ በተቋሙ ውስጥ ብዘኃነትን በተላበስ መንገድ ይዘቶችን ቀርጾ በርካታ ቋንቋዎችን ተጠቅሞ ተደራሽነቱን በይበልጥ ለማሳካት በዜና፣ በፕሮግራም እና በመዝናኛ ዘርፎች እያከናወናቸው ያሉትን ዘርፈ ብዙ ስራዎች አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሔር አድንቀዋል።
የኢትዮጵያ የብልጽግና መስታወት፣ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና፤ የዓለም የስበት ማዕከል የሆነችውን አዲስ አበባን ለማስተዋወቅ ከኢቢሲ ጋር በቅርበት ለመስራት መወሰናቸውንም አቶ ሀፍታይ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን ከኋላ ቀርነት ወደ ብልጽግና ማማ እንድትወጣ ህዝቡን በማነሳሳት፣የመንግስትና የፓርቲውን ስራዎች በተቀናጃና በተደረጀ መልኩ ሰርቶ ለአድማጭ ተመልካች ማሳየት ዋናውና የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን አቶ ቢኒያም ኤሮ ጠቁመዋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀፍታይ ገ/እግዚአብሔር የተመራው የልዑካን ቡድኑ አባላት ሸጎሌ የሚገኘውን የኢቢሲ ሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎብኝቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.