ከአዲስ አበባ የግብር አሰባሰብና የገቢዎች አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ማንኛዉም አይነት ቅሬታ መፍታት የሚያስችል አዲስ አሰራር በከንቲባ ፅ/ቤት ስር ተዋቅሯል ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ ስር የተዘረጋዉ የቅሬታ አፈታት ስርዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በዛ ያልረካ ግብር ከፋይ ከንቲባ ፅ/ቤት ማንኛዉንም አይነት ከገቢ አሰባሰብ ፣ ከሰራተኞች ስነምግባር እና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚነሱ የግብር ከፋዮች ቅሬታዎችን ለመፍታት ዘወትር ሐሙስ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚደመጥ እና ተጣርቶ ምላሽ የሚሰጥበትን አሰራር ዘርግቷል ።
ሁልጊዜም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የሚተጋዉ እና ህዝብን አዳምጦ ምላሽ መስጠትን የትኩረት ማእከሉ ያደረገዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከንቲባ ፅ/ቤት በሚስጥር ጥቆማ የሚሰጥበትን ነፃ የጥሪ ማእከል 9977 ፣ የሚስጥር ሳጥንን ጨምሮ በተጨባጭ ቅሬታዉን በአካል ለበላይ አመራር ማቅረብ የሚችልበትን አሰራር የፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ወደ ተግባር ይገባል ።
በመሆኑም ከመጪዉ ሐሙስ ህዳር 25/2018 ጀምሮ ጠዋት ከ 2 ሰአት እስከ 7 ሰአት ድረስ ከገቢዎች ጋር ብቻ የተያያዘን ቅሬታ አመራሩ ተቀብሎ የሚስተናግድ መሆኑን በመረዳት በከንቲባ ፅ/ቤት ተጨባጭ ቅሬታ ያላችሁ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የከተማዉ አስተዳደር ያሳዉቃል ።
አስተዳደራችን ለቀልጣፋ እና ፍትኃዊ አገልግሎት ይተጋል !
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.