የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ዉድነት እና የዋጋ ንረትን ለመከላከል የሠንበት ገበያ ቦታዎችን እና በአምስቱም በር የገብያ ማእከላትን በመገንባት የንግድ ማህበረሰብ በቀጥታ ከሸማች ማህበረሰብ ጋር እንዲገናኝ ለማድረግ እና ጤናማ የግብይት ስርዓት እንዲኖር እየሰራ ይገኛል::
በተጨማሪም አሰራርና አደረጃጀት በመዘርጋት የድጋፍ የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎችን በወጥነት በማጠናከር ተጨባጭና ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ማምጣቱ ይታወቃል::
በመሆኑም በክፍለ ከተሞች በተደረገው የመስክ ምልከታ እና ነጋዲዉ ና ሸማቹ በሰጡት አስተያየት በሁሉም የሠንበት ገበያዎች የፋብሪካ እና የግብርና ምርት ዉጤቶች በብዛትና በጥራት የሚቀርብባቸዉ እና ሸማቹ እና ነጋዴዉ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ያለምንም ችግር ግብይት የሚፈፀምባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪም የገበያ ቦታዎቹ በአቅራቢያቸዉ የሚገኙ በመሆናቸዉ ከአላስፈላጊ ወጪ እና ላልተገባ እንግልት እንዳይዳረጉ ዕድል የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው ገበያዎችን የማስፋፋት ስራዎች እንዲሁም የድጋፍ፣ክትትልና ቁጥጥር ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ሲሉም ተናግረዋል።
እነዚህ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች የህብረተሰብን አቅም እና ወቅታዉ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ፤ ሠፊ አማራጮች የሚቀርብባቸዉ መሆኑን ገልፀዉ ይህም ሁሉም በአቅሙ የሚስተናገድባቸዉ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት የተረጋገጠባቸዉ ስለመሆናቸዉ አሁናዊ እዉነታዎቹ ማሳያ ናቸዉ ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.