በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ በሚል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ በሚል ርዕስ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች የሚሰጠው ሶስተኛው ዙር ስልጠና በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በኦረንቴሽን ተጀምሯል!

"በመደመር መንግስት እይታ  የዘርፎች እመርታ !"

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በኦሬንቴሽን ፕሮግራሙ ላይ እንዳስገነዘቡት ስልጠናው በአመራሩ መካከል መቀራረብን በማጠናከር ፣ ተቀራራቢ አቅም በመገንባት የሚሰጡትን ተልዕኮዎች ሁሉ በብቃት የሚከውን ሁለገብ አመራር ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልፀዋል።

ለስልጠናው የተመረጡት ጥልቅ ርዕሰ ጉዳዮች ብዝሀ ኢኮኖሚን ታሳቢ ያደረጉ ሀገራዊ መዋቅራዊ ሽግግሮችን ለማጠናከር የተቀናጀና የተናበበ ርብርብ ለማድረግ እንደሚያስችሉ አቶ ሞገስ አስገንዝበዋል።

የብልፅግናችን መዳረሻ የሆነው ከተሜነት ከለውጡ ወዲህ ከፍተኛ ዕድገት ማሳየቱን የጠቆሙት አቶ ሞገስ ውስብስብ የሆኑ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን አቀናጅቶ ለመምራት አቅም የሚፈጠርበት መድረክ በመሆኑ በጥብቅ የአመራርነት ዲሲፕሊን መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ለሚቀጥሉት ስምንት ቀናት ከሚቀርቡ ገለፃዎች ባሻገር በቡድን ውይይት እና በፕሮጀክቶች ጉብኝት በሰልጣኞች መካከል ተቀራራቢ አቅም ለመፍጠር ጥረት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

በኦረንቴሽን ፕሮግራሙ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ም/ ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ  ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራው ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እና ሌሎችም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ሰልጣኝ አመራሮች ተገኝተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.