አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ በፍጥነት እና በጥራት መሃል ፒያሳ ላይ የገነባውን ባለ 11 ወለል ዘመናዊ ህንፃ በዛሬው እለት መርቀን ስራ አስጀምረናል ።
ከተማችን ጀምሮ የመጨረስ እና ቃልን በተግባር የመፈፀም ማሳያ በመሆኗ በየሳምንቱ አዳዲስ የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚረጋግጡ ውጤቶችን እያበሰረ ነው።
አዲስ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ የከተማዋ ወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረገ ያለ፤ በተኪ ምርት ፣ የውጭ ምንዛሪ ሊያስገኙ የሚችሉ ምርቶችን ማምረት ፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን እያስፋፋ ያለ አማራጭ የፋይናንስ አገልግሎት ነው።
አዲስ የተገነባው ህንፃ ለባንክ፣ ለኢንሹራንስ እና ለቢሮ አገልግሎት ምቹ ሆኖ የተገነባ ሲሆን፤ የህፃናት ማቆያ፣ የአካል ማጎልበቻና ካፍቴሪዎችን ጨምሮ ለሰራተኞች ምቹ የስራ ከባቢ እንዲሆን ተደርጎ ተገንብቷል ።
ለውጤታማነቱ የለፋ የቦርድ አባላት፣ የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ፣ ኮንትራክተር እና አማካሪውን በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ፤ ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.