የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡
በዚህ መሰረት፦
1ኛ. የሁሉንም ስፓርት መሰረተ ልማቶችን ለከተማዉ ነዋሪ ተደራሽ ለማድረግ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ አነስተኛ ክፍያ ተመን እና በነፃ መጠቀም የሚቻልበት አሰራር ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል::
2ኛ. የጤና ተቋማት የሥራ አማካሪ ቦርድ ማቋቋሚያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳተላልፏል፡፡
3ኛ.በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) የሚተዳዳሩ ሆስፒታሎች የቦርድ የውስጥ አሰራር ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡
4ኛ. ሃገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ምደባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.