ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ-ብሄራዊ አንድነት
የዘንድሮው የብሄር ብሔረሰብ ሕዝቦች ቀን ለየት ባለ አንፀባራቂ ድል ታጀቦ ህዝቡ ደስታውን የገለፀበት፣ወንድማማችነት እና እህትማማችነት በሕዝቡ ውስጥ የሰረፀበት እንዲሁም ኢትዮጵያዊነት ይበልጥ ነግሶ የታየበት በዓል ነው ፡፡ምክንያቱም ለዘመናት በህዝብ ልብ ዉስጥ ተስፋ ተሰንቆ ሲጓጓለት የነበረው እና የኢትዮጵያን ከፍታ ያረጋገጠው የታላቁ ህዳሴ ግድብ በስኬት የተጠናቀቀበት ማግስት መከበሩ፣የኢትዮጵያን ማንሰራራት የሚያበስሩ የተለያዩ ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች በታወጀበት እና መላውን ኢትዮጵያዊያንን በማሰባሰብ አንድነታችን ጎልቶ በወጣበትና ባሳየበት ወቅት መከበር በመቻሉ ነዉ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.