"ከተማ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ የመልማት አቅም ማሳያዎች ናቸዉ ፡፡"በጉብኝቱ የተሳተፉ ሰልጣኝ አመራሮች
"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ "በሚል መሪ ቃል በሁለተኛ ዙር በአዲስ አበባ ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በአዲስ አበባ ከተማ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ጎበኙ፡፡
የወንዝ ዳርቻዎች፤አዲስ የመሶብ የአንድ ማእከል ዲጂታል አገልግሎት፤የዘዉዲቱ ሆስፒታል ማስፋፊያ ማእከል፤ልፍቶ ሁለገብ የገበያ ማእከል፤የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና ሳይንስ ሙዚየም እና በዘጠኝ ወራት ዉስጥ ተገንብተዉ የተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በጉብኝቱ የተካተቱ እና እየተጎበኙ የሚገኙ ይገኛሉ ፡፡
ሰልጣኝ አመራሮች እስከ አሁን ባደረጓቸዉ የመስክ ጉብኝቶች እንደተናገሩት የከተማ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያ የመልማት አቅም ማሳያዎች መሆናቸው በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.