ቅድምያ ለዜጎች መርሕን በተግባር ያረጋገጡ የከተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቅድምያ ለዜጎች መርሕን በተግባር ያረጋገጡ የከተማችን ተጨማሪ ድምቀት የሆኑት የጋራ መኖርያ ቤቶች!

በውቧ፣ ፅዱና ለመኖር ምቹ ከተማችን አዲስ አበባ፣ ከተማዋን ካደመቁ፣ ካዘመኑ ዘርፈ-ብዙ፥ መልከ-ብዙ የልማት ስራዎች ጎን ለጎን፣ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የተገነቡ የጋራ መኖርያ ቤቶች አካል የሆነውን እና በአጭር ጊዜ በጀርመን አደባባይ፣ በአየር ጤና እና በግራር አካባቢ የተገነቡ 1 ሺ 287 የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተመርቋል።

በተለይ ከለውጡ ወዲህ በተለያዩ የግንባታ ሞዳሊቲ በኮንደሚኒየም 139.008፣ በበጎ ፍቃድ የተገነባ 40,576 ፣ በከተማ አስተዳደር ለኪራይ የተገነቡ 24,819 እንዲሁም ከ 175,605 በላይ የሚሆኑት በሪልስቴት፣ በማህበር እና በግል አልሚዎች የተገነቡ በድምሩ 380,000 ቤቶች ተገንብተው ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል የችግረኞች እምባ ታብሷል በተጨማሪም ለሰው ክብር ከማይመጥኑ ስፍራዎች ዜጎችን በማንሳት በክብር የቤት ባለቤት አድርጓል።

በቀጣይም የከተማዋ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ለማሻሻል ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አማራጮች በመቅረጽ ስራ ተጀምፘል። በተለይም የግሉን ዘርፍ ወደ ሥራ በማስገባት ከሚሰራው በተጨማሪ፣ ለስራው ፍጥነትና ጥራት ተጨማሪ አምስት አማራጮችን በመከተል ወደሥራ ተገብቷል።

በግልና በመንግስት ጥረት በፍጥነት ከተገነቡትም በጀርመን አደባባይ፣ በአየር ጤና እና በግራር አካባቢ ተገንብተው የተመረቁት የመኖሪያ ቤቶች ማሳያ ናቸው።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.