እዉነትም የስህበት ማዕከል፥ አዲስ አበባ!
የዓለም አይንና ቀልብ ያረፉባት፣ በአንድ ልብ–በአንድ ልሳን በዓለም መድረክ የናኘች፣ ትናንት–ዛሬንና ነገን አስተሳስራ በሕበረ-ብሔራዊነት ቀለም ደምቃ፣ እንደ ስሟ ዉብ አዲስ አበባ እዉነትም የስህበት ማዕከልነቷን ዛሬም በ 25ኛዉ ታላቁ ሩጫ ማስመስከር ችላለች።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህን ለ25 ዓመታት የዘለቀዉን ታላቁ ሩጫ አንዱ የገፅታችን መገንቢያ፣ የአንድነታችንና የአብሮነታችን ማሳያ፣ የአብሮ የመበልፀግ መስፈንጠሪያችን በመሆኑ፤ ለስፖርቱ ዘርፍ ቀጣይነት ባለው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል። እነሆ ዛሬም በዓለም አደባባይ የጀግኖች አትሌቶቻችንን ገናና ታሪክ በማወደስ፣ ትዉልድን የሚያንፁ ዘርፈ-ብዙ የልማት ስኬቶችን እና የመዲናዋን ገፅታ በማጉላት ሃገራዊና ህዝባዊ ተልዕኮዉን እየተወጣ ይገኛል፡፡
እንደ ታላቁ ሩጫ የሩብ ክፍለ ዘመን የአንድነት ጉዞአችን፥ የጀመርነዉን ፈጣን እድገት ይበልጥ ለማሳለጥ እና በዘመናችን ታሪካዊ አሻራችንን ለማስቀመጥ ከመቸዉም ጊዜ በላይ የጋራ ትጋት፣ ፍጥነት እና ፈጠራ የታከለበት ስራ መስራት በዓለም መድረክ ልዕልናችንን እንድናልቅ ይጠበቃል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!
ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇👇
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.