25ኛው የሶፊ ማልት የታላቁ እሩጫ በሠላም መጠናቀቁ የአዲስ አባባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
መነሻና መዳረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ የተካሄደው 25ኛው የሶፈ ማልት ታላቁ ሩጫ ውድድር በሠላም ተጠናቋል፡፡
የውጭ ሀገር ዜጎች ፣ አምባሳደሮች ፣ ታዋቂ ሰዎች እና በርካታ ህዝብ የታደሙበት ከተማችን አዲስ አበባ ለ25ኛ ጊዜ ያስተናገደችው ሩጫ በስኬት ተጠናቋል፡፡ ፕሮግራሙ በአግባቡ እንዲከናወን የፀጥታ ተቋማት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ በመግባታቸው እና በያዝነው ዓመት ህዝብ በስፋት ወደ አደባባይ በመውጣት የታደመባቸው ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች በስኬት ማጠናቀቅ እንደተቻለ የሚታወቅ መሆኑን ፖሊስ አስታውሷል፡፡
የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው ሩጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ድጋፍ ላደረጉ እንዲሁም መሰል ፕሮግራሞች ሲዘጋጁ ሆነ የከተማውን ፀጥታ ለማስጠበቅ በሚሰሩ ስራዎች ነዋሪው እያደረገ ላለው አስተዋፅኦ እና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ ተቋማት አመራሮችና አባላት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በፀጥታ ተቋማት ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.