ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቡድን 20 ተሳ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቡድን 20 ተሳታፊ ከሆኑ የቡድኑ አባላት ጋር ፍሬአማ ውይይት አድርገዋል።

👉 ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ ትብብር፣ የጋራ ትኩረት በሚሹ የባለብዙወገን ጉዳዮች ብሎም ትብብራችንን በሚያጠናክሩ እና ዘላቂ እድገትን በሚያሳድጉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ተወያይተናል።

👉በቡድን ሃያ መሪዎች ስብሰባ ፍሬያማ እና ትርጉም ያላቸው ተጨማሪ ውይይቶችን ከህንድ፣ ቬይትናም፣ ደቡብ ኮሪያ እና አውስትራሊያ መሪዎች ጋር አካሂደናል።
👉በቡድን 20 የመሪዎች ጉባኤ ከኢንዶኔዥያ ምክትል ፕሬዝደንት ጊብራን ራክቡሚንግ ራካ ጋር መልካም ውይይት አድርገናል። በሁለቱም ሀገሮቻችን ቅድሚያ በምንሰጠው በንግድ እና በምግብ ሉዓላዊነት ላይ ባተኮረ የግብርና ማዘመን ሥራ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶች ላይ ተነጋግረናል።
👉ከዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታመር ጋር ተገናኝተን በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ጠንካራውን እና ለረጅም ዘመናት የቆየውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደፊት ማራመድ በማስፈለጉ ላይ ተወያይተናል።
👉ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት እና ከኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ አጄይ ባንጋ ጋር መወያየት ሁልጊዜም ቢሆን አስደሳች ነው። በመካሄድ ላይ ስላሉት በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተናል። ይኸውም በጤና፣ በኃይል ምንጭ እና የአየር ንብረት ጥበቃ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ጉዳይን የተመለከተ ነበር።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.