ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በጆሃንስበርግ የቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ ተገኝተዋል። #aa_prosperity


"በቡድን 20 ጉባኤ ጎን ለጎን ከIMF ፕሬዝደንት ክሪስታሊና ጂኦርጂየቫ ጋር በአለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያዎች ፣ በሀገራችን የኢኮኖሚ ሪፎርም እንዲሁም ዘላቂ እና አካታች እድገትን ለመደገፍ ትብብራችንን ለማጠናከር ስላሉ እድሎች ላይ ተወያይተናል። ለIMF የዘለቀ ግንኙነት ምስጋናዬን እያቀረብኩ የጋራ ትኩረቶቻችንን ለመፈፀም መነሳታችንንም እገልጻለሁ"።

"ከአዲሱ የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ሲዲ ኡልድ ታህ ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል። ውይይታችን ባንኩ በመላው አፍሪካ አካታች እድገት እንዲኖር የሚያደርገውን ወሳኝ ሚና ያጠናከረ ነበር"።

ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን የአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ ሼክ ካሌድ ቢን መሃሙድ ቢን ዛይድ አልናህያን ጋር የመወያየት እድል አግኝተናል። ውይይታችን ስትራቴጂካዊ ትብብራችንን በማጠናከር ለበለጠ የጋራ ርምጃ እድሎችን መመልከት ላይ ያተኮረ ነበር።

ከቱርክዬ ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በኢኮኖሚ፣ የባሕል ወዳጅነት ግንኙነት፣ ዘላቂ ልማት፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን በሚያካትቱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር በቀጠናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር፣ እና በሁለትዮበትምህርት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እና በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ተወያይተናል። ውይይታችን የሁለትዮሽ ትስስራችንን እና የጋራ ጥቅም ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያለንን አቋም ያጠናከረም ነበር።
የኢትዮ-አውሮፓ ኅብረት ግንኙነት ለማላቅ ከአውሮፓ ኅብረት ምክርቤት ፕሬዝደንት አንቶኒዮ ኮስታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በተለያዩ ዘርፎች ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር አቋማችንን እንደገና አጽንተናል።
የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት እየተከናወኑ ባሉ ትብብሮች መጠናከሩን ቀጥሏል። በዚህ ረገድም ከፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ትብብሮቻችን ስላሉበት ደረጃ ተነጋግረናል።
የጀርመን ቻንሰለር ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር ተገናኝተን ተወያይተናል። ውይይታችን በቁልፍ የጋራ ፍላጎት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ትስስራችንን ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶችን ለመፈለግ ያለንን ፍላጎት ገልጸናል።
ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስተር ጋር በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ ትብብር፣ የጋራ ትኩረት በሚሹ የባለብዙወገን ጉዳዮች ብሎም ትብብራችንን በሚያጠናክሩ እና ዘላቂ እድገትን በሚያሳድጉ የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ተወያይተናል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.