እንኳን ለታላቁ ሩጫ 25ኛ ዓመት አደረሳችሁ! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሄር
እንግዶቻችን እንኳን ወደ ውቢቷ ከተማችሁ በሰላም መጣችሁ።
"ታላቁ ሩጫ ከተማችን ለቱሪዝም የሰጠችውን ልዩ ትኩረት ተጨማሪ ድምቀትና መስህብ በመሆን፣ ለማህበራዊ መስተጋብር መጠናከር፣ ለህዝቦች አንድነት ፣ አብሮት እና የባህል ትስስር የላቀ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡
"የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሄር
ኃላፊዉ ይህን የተናገሩት ህዳር 14/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደዉን 25ኛ የታላቁ ሩጫ ዉድድር አስመለክቶ በዛሬዉ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነዉ፡፡
ታላቁ ሩጫ ላለፉት በርካታ ዓመታት የከተማችንን ዉበት በድምቀት ለዓለም ሲያስተዋዉቅ መቆየቱን ገልፀዉ፣ ከተማችን ለቱሪዝም የሰጠችውን ልዩ ትኩረት ተጨማሪ ድምቀትና መስህብ በመሆን፣ ለማህበራዊ መስተጋብር መጠናከር፣ ለህዝቦች አንድነት ፣ አብሮት እና የባህል ትስስር የላቀ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደስሟ ባበበችው እና በደመቀችዉ ዉብ መዲናችን ታላቁ ሩጫ መካሄዱ፣ ከተማችን ይበልጥ የቱሪስት መዳረሻ እና የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማእከልነቷ ይበልጥ የሚያሰፋ እና ለዜጎች ምቹ ከተማ እንድትሆን ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ሲሉ ኃላፊዉ ገልፀዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ምቹ የሆኑና የስፖርት ቱሪዝምን የሚጠናክሩ በርካታ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን ጠቅሰው፤ እነዚህን ስራዎቻችንን በዓለም ደረጃ ለማስተዋወቅና ከፍ ለማድረግ ታላቁን ሩጫ እና መሰል ዝግጅቶችን በትብብር አጠናክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በታላቁ ሩጫ ለመሳተፍ ከተለያዩ ዓለም የመጣችሁ ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ታዋቂ አትሌቶች ከመቼውም ጊዜ በላቀ በደመቀችዉ ውብ እና ፅዱ ከተማችን አዲስ አበባ እየተዝናናችሁ እና የተሰሩ ሰፋፊ መሰረተ-ልማቶችን እየጎበኛችሁ ለዓለም እንድታስተዋዉቁ ሲሉ በከተማ አስተዳደሩ ስም ጥሪያቸዉን አስተላልፈዋል፡፡
ለከተማዋ ነዋሪዎችም በተለመደዉ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣ ተሳታፊዎች በሚመጡበት መንገድ በማበረታታት ተጨማሪ ድምቀት እንድትሆኑ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ለአዘጋጆች እና አስተባባሪዎች፣ ታላቋ ኢትዮጵያ እና አትሌት ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.