ዛሬ ማለዳ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ማለዳ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ፖሊስ ኮሌጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም ያሠለጠናቸውን እጩ መኮንኖች መርቀናል።

ተመራቂ መኮንኖች፣ ለዚህ ትልቅ ስኬት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ በስልጠና ያገኛችሁት ተጨማሪ አቅም  ከማህበረሰቡ፣ ከሌሎችም የፀጥታ ተቋማትና የሙያ ባልደረቦቻችሁ ጋር በመቀናጀት የከተማችንን ሰላሞና ፀጥታ የምታፀኑበት እንደሚሆን  እምነት አለኝ።

ውድ ተመራቂ መኮንኖች፤ ወደ ሥራ ስትሰማሩ ሙያችሁን በታማኝነት፣ በቅንነት፣ ለእውነት በመወገንና በአርቆ አሳቢነት በመመራት ሐቀኛ የሕዝብ አገልጋይነትን በብቃት እንድትወጡ አደራ እላለሁ።
የከተማ አስተዳደሩ ኮሌጁ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ለመሆን ለሰነቀው ራዕይ እንደ ሁልጊዜውም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.