ጥራት ያለው መንገድ የሰለጠነ ከተማ መገለጫ ነው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጥራት ያለው መንገድ የሰለጠነ ከተማ መገለጫ ነው!

መዲናችን አዲስ አበባ፣ እያደገ በመጣዉ የተሽከርካሪ ቁጥር እና በነበረው የመንገድ እጥረትና ጥራት ችግር  ምክንያት ለትራፊክ መጨናነቅ ተጋላጭ ሆና ቆይታለች::

ችግሩን የተገነዘበዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከለዉጡ ማግስት ጀምሮ፣ የረጅምና የአጭር ጊዜ ዕቅድ በመተለም፣ የትራንስፖርት ዘርፉን ታሪክ የቀየረ፣  
ምቹ እና የተሳለጠ የመንገድ ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች እና ተርሚናሎችን በስፋት ገንብቶ ችግሩን ከምንጩ ለመፍታት የላቀ ስራ ሰርተል።

በከተማዋ ከመሬት በታች ጭምር ተገንብተዉ የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ደረጃቸዉን የጠበቁ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ እና ተርሚናሎች በአንድ ጊዜ ከ1ሺ በላይ መኪና በማስተናገድ፣ የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ፣ የትራንስፖርት ፍሰትን በማሳለጥ፣ የመንገድ ደህንነትን በማስጠበቅ፣ የትራፊክ አደጋን በመቀነስ፣ የጊዜና የነዳጅ ብክነትን በማስቀረት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ እና ለዜጎች የስራ-ዕድል በመፍጠርና  ምርታማነትን በማሳደግ ከተማዋን ዘመናዊ ገፅታ ያላበሱ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ናቸዉና ልንጠብቃቸዉና ልንጠቀምባቸዉ ይገባል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.