ሩጫ በኢትዮጵያ ትልቅ ታሪክና ቦታ አለው። ላለፉ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሩጫ በኢትዮጵያ ትልቅ ታሪክና ቦታ አለው። ላለፉት 65 ዓመታት ኢትዮጵያ በርካታ የረጅም ርቀት ሯጮችን ለዓለም አበርክታለች።

እንኳን ደስ አለን !!

 አበበ ቢቂላ በ1952 ዓ.ም  በጣሊያን መዲና ሮም በተካሄደው 17ኛው የኦሊምፒክ ማራቶን ውድድር ላይ በባዶ እግሩ በመሮጥ እና የወርቅ ሜዳሊያን በማግኘት ታሪካዊ ድል ማስመዝገቡን በመከተል በተለያዩ ወቅቶች የተለያዩ ጀግና አትሌቶች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርገዋል።

የአትሌት አበበ ቢቂላ ድል እና ላለፉት 25 ዓመታት የመዲናችን ብሎም የኢትዮጵያ መገለጫና ተናፋቂ የአደባባይ ስፖርታዊ ክንውን የሆነው “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” የዓለም አትሌቲክስ ቅርስነት እውቅናን ተቀብለዋል።
ይህ እውቅና በስፖርቱ ዘርፍ የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያጎላ ነው።

ጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላን፣ የታላቁ ሩጫ ውድድር መስራች  የሆነውን ጀግናው አትሌታችን ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴን እና ይህን ውድድር ባለፉት ዓመታት ባማረ ሁኔታ ሲያካሂዱ የቆዩትን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማመስገን እወዳለሁ።

በቀጣይም ውድድሩን ከዚህም በበለጠ ለማሳደግ እና ብዙ የውጭ ሀገር ተሳታፊዎችን ወደ ከተማችን እንዲያመጣ ለማድረግ የበለጠ ተባብረን የምንሰራ ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.