በሰውስራሽ አስተውሎት ዘርፍ ለመሰማራት ሃሳብ ፣ ፍላጎት ኖሯችሁ በተለያየ ምክንያት እድሉን ያላገኛችሁ የከተማችን ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች በተመቻቸዉ የነፃ እድል እንድትጠቀሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለኢትዮዽያዊያን የኩራት ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባዉን የኢትዮዽያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት የለውጥ አመታት በአገራችን ከታዩ የማድረግ አቅሞች መካከል አንዱ የሁሉም ፣ በሁሉም የሆነችዉ የአዲሷን ኢትዮዽያ ተልዕኮ መሸከም የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት ነዉ ብለዋል።
የተቋማት ግንባታ ማሳያው ደግሞ የኢትዮዽያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዱ ነው ። አጠቃላይ በተቋሙ የተመለከትነዉ ሁሉ እጅግ አስደናቂ ነዉ።
በዚህ የዉድድር አለም እንደ አገር ሉአላዊነትን አስጠብቆ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት በየትኛዉም መስፈርት የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል ።
ይህንን እዉነታ ከአመታት በፊት አስቀድሞ በመረዳት ለዚህም አገራዊ ተልዕኮን በብቃት የሚያሳካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አቅም ያለዉ ተቋም በአጠረ ጊዜ እዉን እንዲሆን ላደረጉት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ለመላዉ የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዘርፉ ለመሰማራት ሀሳብ ፣ ፍላጎት እያላችሁ በተለያየ ምክንያት እድሉን ያላገኛችሁ የከተማችን ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ተቋሙ ባመቻቸዉ የነፃ እድል እንድትጠቀሙ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.