በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ በሚል ርዕስ የሚሰጠው ስልጠና እንደ አዲስ አበባ በጋራ ኦሬንቴሽን ተጀምሯል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በኦሬንቴሽን ፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በየወቅቱ የሚሰጡ ስልጠናዎች በፓርቲያችን እሳቤዎች ፣ በመንግስት ፖሊሲዎች እና አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት እሴቶች እንዲጎለብቱ ማስቻላቸውን ጠቅሰዋል።
ከነገ ጀምሮ ለስምንት ቀናት በሚሰጠው ስልጠና የመደመር መንግስትን እይታ ከዘርፎች እመርታ ጋር ተሰናስኖ እንደሚቀርብ ያብራሩት አቶ ሞገስ አገልጋይ እና ሁለገብ አመራር ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት አጋዥ እንደሚሆን ገልፀዋል።
ስልጠናው የአመራሩን የአስተሳሰብ አንድነት እንደሚገነባ የጠቀሱት አቶ ሞገስ የሚኖሩ የቡድን ውይይቶችም በፌዴራል ተቋማት እና በከተማችን አመራሮች ዘንድ ቅርርብን እንደሚያጠናክሩ አስገንዝበዋል።
ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊ ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ተተንትነው የሚቀርቡበት ነገ የሚጀምረው ስልጠና ግቡን እንዲመታ በዲሲፕሊን በመከታተል ፣ እርስ በእርስ በመማማር ተቀራራቢ አቅም ይዞ መውጣት እንደሚገባም አቶ ሞገስ አሳስበዋል።
"በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ " በሚል ርዕሰ እንደ ሀገር በሁለተኛ ዙር በሚሰጠው ስልጠና በአዲስ አበባ ከ 2ሺህ በላይ ከፌዴራል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች የሚሳተፉበት ሲሆን ፤ በስልጠናው ማጠቃለያም ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.