ዜጋ ተኮር መሰረተ ልማት ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዜጋ ተኮር መሰረተ ልማት ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫችን ነው!!

ፒያሳ እና ካዛንቺስ እጅግ በተጨናነቁና ለመኖር አስቸጋሪ በሆኑ መንደሮች ውስጥ ሲኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች በተለይም በተጣበቡና በተጎሳቆሉ፣ ለኑሮ ምቹ ባልሆኑ የሰውን ክብር በማይመጥኑ ቤቶች ዉስጥ ህይወትን መግፋት ለበርካቶች የዕለት ተዕለት ህይወት መሆኑ አይዘነጋም፤ ዛሬ ግን ታሪክ ሆኖ አልፏል! 

የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር “ከተማን ማልማት፣ መሰረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ህይወት ማሻሻል ነዉ!” ብሎ በፅኑ በማመን እና ለልማት ተነሺዎች ፤ለተለያዩ ችግሮች ለተጋለጡ፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአገር ባለውለታዎች እና በወንዝ ዳርቻዎች ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢዉን ትኩረት በመስጠት፣ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከለ የቤት አማራጮችን  በመዘርጋት በርካታ ቤቶችን ገንብቶ ለነዋሪዎች ማሰረከብ  ችሏል፡፡

የተገነቡት ቤቶች  የከተማዋን  ጎስቋላ ገፅታ  የቀየሩ ፣ የዜጎችን እምባ ያበሱ፣ ሰፋፊ የስራ ዕድል የፈጠሩ እና አገልግሎቶችን ያሳለጡ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የህብረተሰቡን ገቢ ማሳደግ የቻሉ ገፀ-በረከቶችም  ናቸው፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.