ኢኮ ቱሪዝም ሌላኛው የከተማችን ድምቀት!

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢኮ ቱሪዝም ሌላኛው የከተማችን ድምቀት!

መንግስት ቱሪዝምን የኢኮኖሚያችን ቁልፍ ዓምድ ቀዳሚ አድርጎ ያስቀመጠው የኢትዮጵያ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ስኬታማ ለማድረግ፣ መንግስት በመዲናዋ  አዲስ አበባ በምናብ ከፍታ፣ በአመራር ትጋትና በህዝባችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ፣ በድንቅ ተፈጥሮ እና በልማት ሥራ እድገት መካከል ያለውን መስተጋብር በማሳለጥ፣ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል፣ እንጦጦ ፓርክ፣ ወዳጅነት ፓርክ፣ አራዳ እና እሬቻ፣ አንድነት ፓርኮች እና ሌሎች ብ..ዙ.. አረንጓዴ ስፍራዎች፣ እንዲሁም በከተማዋ መሃልና ዙሪያ ያሉ ተፋሰስ ወንዞችን እና  የኮሪደር መሰረተ-ልማቶች እና  የቅርስ ልማት ለአዲስ ሌላው ድምቀት፣ ለቱሪስት ስሕበት  እንዲሁም ለአየር ንብረት ለዉጥ  የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ይህም፥ ከህንፃ፣ መንገድ እና መሰል ዘርፈ-ብዙ መልከ – ብዙ የኮረደር መሰረተ-ልማቶች ውብ እና ለመኖር ምቹ ሥሉጥ ከተማ (Smart City) መገንባታችን የሚያያረጋግጥ ነው፡፡  ለዚህም ነው ስለከተማችን ዓለም በእንድ ድምፅ ያወራላት፣ ያረጋገጠላት፡፡ 

ማሳያውም ኢትዮዽያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ አንዱ ነው፡፡ ባህል እና ስልጣኔን ከተፈጥሮ ጋር ያዋኻዱ  የኢኮ-ቱሪዝም መሰረተ-ልማት ገፆች እንካችሁ ብለናል::

እንወቃቸው፥ እንጎብኛቸው!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.