የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ እና የገበያ ግሽበትን ለማረጋጋት እያደገ በመጣዉ ጤናማ የግብይት ስርዓት በመዲናዋ አምስት በሮች በገነባቸዉ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች መሸጫ እንዲሁም እየሰፉ በመጡ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በርካታ ስራዎችን ሰርቷል።

በተለይም የደላሎችን ሰንሰለት በመበጣጠስና የገበያ ሰንሰለቱን በማሳጠር ሸማቹ የከተማ ነዋሪ በቀጥታ ከአርሶ አደሩና ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚገናኝበት ፣ሁሉንም ምርቶች በአይነትና በጥራት እንዲሁም ተመጣጣኝና ፍትሀዊ በሆነ የዋጋ አማራጮች የሚያገኝበት እድል ተፈጥሯል ።

በእነዚህ ማዕከላትና የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ጎራ ብለው በአቅምዎትና በፍላጎትዎ እንዲሸምቱ ተጋብዘዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.