ዛሬ በይፋ መርቀን ስራ ያስጀመርነው የዘዉዲቱ መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በይፋ መርቀን ስራ ያስጀመርነው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የላቀ የሕክምና ማዕከል ዓለም አቀፍ ጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ ዘመኑን የዋጀ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥን የሚያሟላ ነው።

በውጪ ሀገራት  ንፁህ እና ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የተሟላላቸዉ የህክምና ማእከላትን ስናይ “ መቼ ይሆን በሃገሬ ይህንን የመሰለ ለባለሙያው፣ ለታካሚው እንዲሁም ለአስታማሚው ጭምር የተመቸ  ዘመናዊ የጤና ማዕከል የሚኖረው?” ለሚለው ቀና ቁጭት ምላሽ የሰጠ ነው።

ይህ የላቀ የሕክምና ማዕከል የተለያዩ አገልግሎቶች የተካተቱበት ሲሆን ፦
•  የተኝቶ ህክምና ህሙማን ክፍሎች (IPD)
•  የጨረር  ህክምና አገልግሎቶች
•  የህፃናት እና የአዋቂዎች ፅኑ ህሙማን ክፍሎች (ICU)
•  የኦክስጅን ማምረቻ ፕላንት
•  የቪአይ ፒ አልጋዎች
•  የኦፒዲ ክፍሎች
•  የኦፕራሲዮን ክፍሎች(OR) እና  የማገገሚያ ክፍሎች እንዲሁም
•  የድንገተኛ ክፍል አልጋዎች
•  በየህክምናው አይነትና በየወለሉ ፋርማሲ እና የመድሃኒት ስቶር
•  ላቦራቶሪ
•  የአስተዳደር ቢሮዎች 
•  የማብሰያ ክፍሎች፣ ዋና  ካፊቴሪያ፣ በየወለሉ ለሚገለግሉ ባለሙያዎች  የሚሆኑ ካፊቴሪያዎች 
• የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ከውብ ምድረ ግቢ ጋር አካቷል፡፡

ይህን ለማሕበረሰባችን ፋይዳው እጅግ የላቀ የጤና ማዕከል  ለአገልግሎት እንዲበቃ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ተቋማት ፣ አመራሮች እና ባለሙያዎችን በተገልጋዩ  ሕብረተሰብ እንዲሁም በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመሰግናለሁ ።

በማዕከሉ የምትገኙ  ውድ ባለሙያዎች፣ ለህሙማን የምትሰጡትን አገልግሎት የሚያቀልላችሁ  የላቀ የሕክምና ማዕከል  እንኳን አገኛችሁ እያልኩ  በአግባቡ እንትጠቀሙበት እና ከምንጊዜውም በላይ ሙያዊ ስነምግባር እና ርህራሄ እንዳይለያችሁ አደራ እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.