ዛሬ በአንጋፋው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታልን የሚመጣጠን ማስፋፊያ ገንብተን፤ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ አሟልተን ስራ አስጀምረናል ።
እንኳን ደስ አላችሁ !!
በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባው የላቀ የሕክምና ማዕከል፣ በ1 ሺህ 800 ካ.ሜ ስፋት ላይ ያረፈ እና ባለ 10 ወለል ህንፃ ሲሆን ለተኝቶ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ 320 አልጋ አለው። ይህም ላለፉት 91 ዓመታት የነበረውን የዘውዲቱ ሆስፒታል ታካሚ አገልግሎትን በእጥፍ ያሳድገዋል።
ሆስፒታሉ ለህክምና ባለሙያው እና ለታካሚው በሚመች መልኩ የተገነባ ሲሆን አሁን ላይ የህክምናው ዘርፍ በደረሰበት ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተደራጀ እና የራሱ ኦክስጂን ማምረቻ ጭምር ያለው ነው።
ይህ ሆስፒታል አስተዳደራችን አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመረው ሥራ ተደማሪ አቅም የሚፈጥር ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.