“በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ”...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ::

ዛሬ “በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በተሰጠው ስልጠና ላይ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እና የፓርቲያችን ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የተቀመጡ ዋና ዋና ግቦችን ወደ እቅድ በመቀየር በከተማችን አዲስ አበባ በላቀ አፈፃፀም እና ውጤታማነት ለመተግበር ከከተማችን አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደናል ።

እንደ ከተማ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ እና ፍጥነት መርህ ግቦቹን ለማሳካት የተዘጋጀውን ዝርዝር እቅድ የጋራ አድርገናል።

ከተለዩት ዋና ዋና ግቦች መካከል የብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባን (የፋይዳ ምዝገባ)፤ የ5 ሚሊዮን ኮደሮችን፤ የተጀመሩ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳር ልማት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን፣ ለምርጫ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ግቦችን መቶ በመቶ ማሳካት፤ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፤ ሌብነት፣ ጉቦኝነትንና ብልሹ አሰራርን፣ በመንደርተኝነትን፣ በአካባቢዊነት ማሰብና መስራትን እና ጠባቂነትን መቀነስ፤ እንዲሁም ተረጂነትንና ልመናን፣ ለልማት መዋል የሚገባውን መሬት አጥሮ ማስቀመጥ፣ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ እና ሰላማዊ ሁኔታን የሚያውኩ የጥፋት እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የዋና ዋና ግቦች የትኩረት ማዕከል ሆነው የሚፈፀሙ ይሆናል።

ግቦቹን ለመሳካትና ለውጤታማነታቸው እንደ ወትሮው ትዉድልድና የተቋምን እየገነባንበ ተለወጠ የስራ ባህል 24/7 በትጋት እና በቁርጠኝነት የምንሰራ ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.