ኢትዮዽያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኢትዮዽያ ከሁለት ዓመት በኋላ የሚካሄደውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን እንድታስተናግድ ብራዚል ውስጥ እየተካሄደ ባለው የዘንድሮ ስብሰባ ላይ ተመረጠች።

በአውሮፓውያኑ 2027 የሚደረገውን "ኮፕ32" ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ የተመረጠችው ናይጄሪያን በመብለጥ ነው።

ኢትዮዽያ ባለፉት 6 ዓመታት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ  አሕመድ አመራር የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ከ48 ቢሊዮን በላይ አገር በቀል ችግኞችን በመላዉ አገሪቱ የተከለች ሲሆን  በተጨማሪም በወንዝ ዳርቻዎች ልማት  ሰፋፊ የአካባቢ ጥበቃ ስራ እየከወነች  እና ግዙፍ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎችን እየገነባች ትገኛለች ።
ኢትዮዽያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ግንባታ  በሰራቻቸዉ ሰፊ  ስራዎች ለአብነት የምትጠቀስ  እና ልምድ የሚቀሰምባት አገር  ሆናለች ።
#COP32 ን ማስተናገድ በብዙ ሺዎች  የሚቆጠሩ ልዑካንን ወደ አዲስ አበባ የሚስብ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ያጠናክራል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.