"በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ 11 ቀናት ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ክቡር የፓርቲያችን ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሰጡት ማጠቃለያ እና የስራ መመሪያ ዛሬ ተጠናቅቋል ።
ክቡር የፓርቲያችን ፕሬዝዳንት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ ፣ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን ይበልጡን ለማስፋት እና ለማላቅ ፣ የሕዝባችንን ሁለንተናዊ የመልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ስራዎችን በፈጠራ እና ፍጥነት መርህ በማብዛት መከወን እንደሚገባ አንስተዋል ።
እንዲሁም በቀጣይ የአመራሩን ትኩረት የሚሹ ግቦችን ጭምር በየፈርጁ በመለየት አቅጣጫ የተቀመጡ ሲሆን አመራሩም በከፍተኛ መነሳሳት ለመፀም ቃል ገብቷል ።
ይህ በአዳማ ከተማ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ከትላንት በስተያ በኦሮምያ እንዲሁም በትላንትናዉ እለት በአዲስ አበባ በፓርቲያችን እሳቤ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት እና ልምድ የመለዋወጥ መርሃ ግብር ጭምር የተካሄደ ነበር ።
በመስክ ጉብኝታችን ያገኘናቸው በርካታ ስኬቶች በምናብ ከፍታ፣ በአመራር ትጋትና በህዝባችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬነት ማሳያ መሰረቶች ናቸዉ ።
የተገኙ ዉጤቶች እንደተጠበቁ ሆነዉ ገና አዳዲስ ነገሮችን እንፈጥራለን! እንፈጥናለን! የኢትዮጵያ ብልጽግና እናረጋግጣለን!!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.