#ማገልገል የህሊና እርካታ የስብዕና አክሊል ነው!
በሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና በደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የእንጠያየቅ መድረክ ተካሄደ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አስተባባሪነት ከክፍለ ከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት እና በደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የእንጠያየቅ መድረክ አካሄደ ።
የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን በከተማዋ በርካታ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ተጨባጭ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን በማንሳት ነገር ግን አሁንም በአገልግሎት አሰጣጡ መሻገር ያልተቻለ የአገልግሎት ማነቆዎች መኖራቸውን ይህም በከተማዋ የመጣውን ለውጥ የሚያጠለሽ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተሰጣቸው ኃላፊነት ማህበረሰቡን በአግባቡ በማገልገል የተገልጋዩን እርካታ ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድ መንግስት የልማት ሆነ የፀጥታና ሌሎች ተግባራትን ብቻውን ማከናወን የማይችል በመሆኑ ህዝቡ እያደረገ የሚገኘውን ድጋፍና ተሳትፎ በማሳደግ የአካባቢው ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ እንዲሁም የህግ መተላለፎችን መከላከል እንደሚገባ በማንሳት መንግስት ማህበረሰቡ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በመፍጠንና በመፍጠር መርህ የሚመልስ መሆኑን ተናግረዋል ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ጽ/ቤት ህዝብና መንግስት ድልድይ በመሆን በርካታ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ በማንሳት መድረኩ ተቋማቱ ማህበረሰቡ የሚየነሳቸውን ችግሮች ፊት ለፊት በመነጋገር ያሉ ክፍተቶችንና የማህበረሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች ለመለየት የዕቅድ አካል በማድረግና ችግሮቹን በመፍታት የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የደንብ መተላለፍ የሚፈፅሙ ከግለሰብ እስከ ተቋማትን ተጠያቂ የማድረግ ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ በዚህም የደንብ ጥሰቶች እየቀነሱ እንደሚገኝና ማህበረሰቡ ማንኛውንም የደንብ ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ተፈፅመው ከተገኙም የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንዲሁም ሰላም የማይጠገብ ትልቅ ሀብት መሆኑንና ማህበረሰቡ የክፍለ ከተማው ሰላም ለማስከበርና የደንብ መተላለፎች እንዳይኖሩ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኙ የገለፁት ተሳታፊዎች በተለያዩ ወረዳዎች የሚስተዋሉ በካይ ፍሳሾች ፣ ህገ-ወጥ ተግባራት ፣ አዋኪ ድርጊቶች እንዲሁም ሌሎች የሰላምና ፀጥታ ችግሮች እንዲፈቱ እንደሚሰሩ የጠየቁ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች የሚመለከታቸው አካላት ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥተዉባቸዋል ።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.