ውጤታማ የንግድ ስርአት እንዲኖርና ተደራሽነቱ የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ውጤታማ የንግድ ስርአት እንዲኖርና ተደራሽነቱ የሰፋ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ከማፍራት አኳያ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ፡፡

አሰራርና ጥራትን ማስጠበቅ ይገባል ሲሉ ደግሞ የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
 
"ውጤታማ የህዝብ ግንኙነት  ለፍትሀዊ ንግድ ግብይት" በሚል መሪ ቃል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት መድረክ አመቻችነት  የእንጠያየቅ  የውይይት መድረኩ  የክፍለ ከተማው ንግድ ፅህፈት ቤትና የህብረት ስራ ፅህፈት ቤት በተገኙበት ተካሄዷል፡፡ 

የምናገለግለው ህዝብ ያለበትን ችግር በማወቅ ለዛም ፈጣን መፍትሄ ለመውሰድ እንዲህ አይነት መድረኮች ትልቅ ሚና አላቸው ያሉት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ ናቸው፡፡ 

አስተዳደሩ ነዋሪውን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ ስራዎችን ይሰራል የህዝብ እርካታ ማምጣታቸውንም ይከታተላል፤ በተደራጀ መልኩ የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነትንም ይሁን የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለማወቅ እንዲህ አይነት መድረኮች ጥቅማቸው ከፍተኛ ነው ሲሉ የእንጠያየቅ መድረኩን አስፈላጊነት ገልፀውታል፡፡  

የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ መረጃን በተለያዩ የኮሙዩኒኬሽን መንገዶች ተደራሽ የማድረግ ስራን ይሰራል ያሉት ደግሞ የክፍለ ከተማው ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ዘይነባ ጣሀ ናቸው፡፡ ፅህፈት ቤቱ መንግስትና ህዝብን የማቀራረብ ስራም በህዝብ ግንኙነት ዘርፉ እየሰራ ነው ይህም መድረክ አንዱ የዛ አካል ነው ያሉት ሀላፊዋ የነዋሪውን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ የሚችሉ ስራዎች በአስተዳደሩ እየተሰሩ ነው በዛ መሀል የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለይቶ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲህ አይነት መድረኮች ሚናቸው የጎላ በመሆኑ ያንን ፅህፈት ቤቱ ከንግድና ከህብረት ስራ ፅህፈት ቤቶች ጋር በመሆን እንዲመቻች ተደርጓል ብለዋል፡፡    

በመድረኩም የክፍለ ከተማው የንግድ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አስቴር ደሳለኝ  እንዲሁም የህብረት ስራ ማሀበር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አልማው ሀይሉ ስለተቋማቸው አጭር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡  
በመድረኩም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተው አለን ያሉትን ጥያቄና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን በተለይም  ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት  አገልግሎትና ተደራሽነት፣ ከሚያቀርባቸው ልዩ ልዩ መሰረታዊ ፍጆታዎች ጥራትና ዋጋ፣ በክፍለ ከተማው ያለው ዩኒዬን የአቅርቦት ሁኔታ፣ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች አጋጣሚዎችን እየተጠቀሙ የሚያደርጉት ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ መኖር፣  የእሁድና ቅዳሜ ገበያዎች የአቅርቦት ሁኔታና መሰል   ተያያዥ  ጥያቄና አስተያየቶች በመድረኩ ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ 

ያሉት ቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በቂ አቅርቦት ይሰጣሉ ያሉት እነዚሁ ተሳታፊዎች በለጠፉት ዋጋ ልክ ግን የመሸጥ ችግሮች በተወሰኑት ላይ ይታያል  ያ ሊስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡ ፅህፈት ቤቱም ይህን ወስዶ እንደሚያርም ወይዘሮ አስቴር በምላሻቸው ተናግረዋል፡፡  የሸማች ማህበራት ሱቆችን ማጠናከርና  በተመጣጣኝ ዋጋ ማህበረሰቡን የሚያገለግሉበት መንገድ መልካም ነው ነገር ግን አቅርቦት ላይ ያለው ችግር ቢፈታ ያሉት ተሳታፊዎች ያንን ፅህፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን እንደሚሰራበት የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ አልማው ሀይሉ በምላሻቸው ተናግረዋል፡፡ 

ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ያልተገባ ዋጋ ጭማሪ ውስጥ ገብተዋል ያሉት ተሳታፊዎቹ ያንን ፅህፈት ቤቱ እያጣራ እርምጃ ቢወስድ ብለዋል  ለዚህም ወይዘሮ አስቴር  ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከስቶር ፍተሻ ጀምሮ እስከ ነጋዴው የተጠናከረ ቁጥጥር እያደረግን ነው ያንን አጠናክረን እንቀጥላለን እርምጃም የተወሰደባቸው አሉ ብለዋል፡፡ 
 
  ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.