አዲስ አበባ ለኑሮ፣ ለስራ እና ለጉብኝት ምቹ ከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባ ለኑሮ፣ ለስራ እና ለጉብኝት ምቹ ከተማ እየሆነች ነዉ :- አቶ ኦርዲን በድሪ

በብልጽግና እሳቤ እና በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የብልጽግና እሳቤዎች በአዲስ አበባ በተጨባጭ እየታዩ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል፡፡

በተለይም ከኮሪደር ልማት አኳያ አዲስ አበባን  እንደ ስሟ ውብ እና የብልጽግና ተምሳሌት እናደርጋለን የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ በአዲሰ አበባ በተጨባጭ  መተግበሩን  አይተናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት አዲስ አበባ ላይ በቂ መሰረተ ልማት አልነበረም፣ የመኖሪያ ቤቶች በጣም የተጎሳቆሉ፣ ለኑሮ የማይመቹ፣ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥኑ እንዲሁም ከፍተኛ ጥግግት ያላቸው እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡

አሁን ላይ ግን ያ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ተቀይሮ ማየት መቻላቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ለኑሮ፣ ለስራ እና ለጉብኝትም ምቹ ከተማ እየሆነች መምጣቷን ነው ያመላከቱት፡፡

ከመሠረተ ልማትም አንፃር በከተማዋ በርካታ የመሠረተ ልማት ስራዎች በአስደናቂ ሁኔታ እየተከናወኑ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.