የሀይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች ለሰላም እሴት ግንባታ ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፁ::
መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ከኮሙኒኬሽን ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል፡፡
የሀይማኖት ተቋማት እሴት ግንባታን አስመልከት ለሃይማኖት ሚዲያ ተቋማት እና ለማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል::
የአዲስ አበባ ሃይማኖት ጉባዔ ዋና ፀሃፊ መጋቢ ታምራት እንደተናገሩት የሀይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች ከተቋቋሙበት ዓላማ አኳያ የማህበረሰቡን እሴት፤ሃይማኖትና ባህል በጠበቀ መልኩ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ መረጃን በማሰራጨት፤የተዛቡ አስተሳሰቦችን በማስተካከል፤ በሃገራዊ እና በማህበራዊ ጉዳዮች ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ከሌሎች ሚዲያ ተቋማት ጋር ተቀናጅቶ መስራት ወሳኝ እና ሃገርን ወደ አዲስ ምእራፍ የሚያሸጋግር የስኬት ጉዞ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል::
ለሃገራዊ ሰላም እሴት ግንባታ በጋራ ተቀናጅቶ በመስራት ሃገራዊ ሃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ ጠቅሰዉ ይህም በሌሎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በሰጡት ማብረሪያ ተናግረዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘዉዱ ከበደ በበኩላቸዉ ከለዉጡ በኋላ መንግስት ለሚዲያ ነፃነት የተሠጠዉን መብት ተጠቅመዉ በከተማችን በርካታ ሚዲያዎች መቋቋማቸዉ ጠቁመዉ በሚዲያቸዉ ስለሀገር አንድነት ስለልማት፤እድገት እና ብልፅግና ያለምንም እረፍት የሚሠሩ ምርጥ የሚዲያ ባለሙያዎችን ያፈራች ሀገር ለመሆን ችላለች ብለዋል።
በሌላ በኩል ይህን የሚዲያ ነፃነት ያልተረዱ ጥቂት የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች በሀይማኖት ስም በግላቸዉ ወይም በተደራጀ መንገድ ከህግ አግባብ ዉጪ በማህበራዊ ሚዲያዉ የሀገራችንን አንድነት በሚያጠለሽ መንገድ ለእኩይ ተግባራት ሲጠቀሙበት ይታያሉ ሲሉ ገልፀዋል፡፤።
በዚች የሁሉም ኢትዮጵያዉያን መናኸሪያ በሆነች ከተማ ሚዲያዎች ለአገር ብልፅግና በተናበበ መንገድ መስራታቸዉ የማያወላዳ ሀቅ መሆኑ የጠቆሙት የኮሙኒኬሽን ም./ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘዉዱ ከበደ በሀይማኖት ተቋማት ስር የሚገኙ የሚዲያ ተቋማትና ባለሙያዎች ይህን የስራ መርህ ለማስቀጠል እና ከዚህ ዉጪ የተሠማሩትን ለመምከርና ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡና እና ተቀናጅቶ የመሥራትን ባህል እንዲጎለብት እድል የፈጠረ መድረክ በመሆኑን ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ ረታ እንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሃገራት መካከል ግንባር ቀደም እና የመላ ኢትዮጵያዊያን መሠብሠቢያ ጌጥ ስትሆን የዚህም ሚስጢሩ በአንድ እጅ ልማት በሌለኛዉ ሰላምን ማዕከል ያደረገ ስራዎችን መስራት በመቻሏ ነዉ ብለዋል።
የዛሬዉ መድረክም ሀገር በቀል የሠላምና መቻቻል እሴቶች ለትዉልድ ግንባታ እና ለፈጣን ልማታዊ እድገት የሀይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች አበርክቷቸዉ የጎላ በመሆኑ በዘመናችን ኢንተርኔትና ተዛማጅ ቴክኖሎጂዎች በመስፋፋታቸዉ ለአንድ ሀገር እና ትዉልድ ጥፋት ወይም ግንባታ ያለቸዉ አቅም እያደገ መምጣቱን ከወዲሁ ተገንዝበዉ ከተቋቋሙበት ዓላማ ከሀገሪቱ የሚዲያ ህግ እና ፖሊሲ ጋር በተጣጣመ መልኩ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር ለሀገረ መንግስት እና ለብሔረ መንግስት ግንባታ ሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል በማለት መልዕክታቸዉን እስተላልፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.