አለርት ሆስፒታል በካይ ኬሚካል ወደ ወንዝ በመልቀቁ አንድ ሚሊዮን ብር ተቀጣ
የመንግስት የጤና ተቋም የሆነዉ አለርት ሆስፒታል በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በወንዝና በወንዝ ዳርቻ በካይ ቆሻሻ በመልቀቁ አንድ ሚሊዮን ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታዉቋል።
ብክለቱ በከተማው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች በላብራቶሪ የተረጋገጠ በመሆኑ ሆስፒታሉ አንድ ሚሊዮን ብር ተቀጥቷል።
በሌላ በኩል በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 በወንዝ ዳርቻ ብክለት የፈፀሙ 6 የተሽከርካሪ እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት (ላቢያጆዎች) እያንዳንዳቸው አንድ መቶ ሺህ ብር በድምሩ 600 ሺህ ብር ተቀጥተዋል።
ባለስልጣኑ በተደጋጋሚ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰራ ቢሆንም ከህገ ወጥ ተግባራቶች በማይታቀቡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የሚወስደው አስተዳደራዊ እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል በመሆኑ ነዋሪዎችና ተቋማት ከመሰል ተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል።
AMN.
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.