የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በስሩ የሚገኙ የሴክተር ተቋማት የኮሙኒኬሽን ዘርፍ የበጀት ዓመቱን የ 3 ወራት እቅድ አፈፃፀም ስራዎችን ገመገመ
ቢሮዉ የ2018 በጀት የ 1ኛ ሩብ ዓመት የሴክተር ተቋማት የኮሙኒኬሽን ዘርፍ እቅድ አፈፃፀም ተግባራትን ገምግሟል።
በግምገማዉም የሴክተር ተቋማት የኮሙኒኬሽን የዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች እና የተቋማት ክላስተር አስተባባሪዎች የበጀት ዓመቱን የ 3 ወራት አበይት እና ቁልፍ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም እንዲሁም የተቋማት የመረጃ አጠቃቀም እና ዉጤታማነት ያለበት ደረጃ ላይ ያተኮረ ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል።
የቢሮዉ ም/ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሶስት ወራት በከተማዋ በርካታና ትላልቅ ስራዎች የተከናወኑበት፤ወቅታዊ፤ፈጣንና ጥራታቸዉን የጠበቁ ትክክለኛ መረጃዎች የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በመጠቀም በተለያዩ የሚዲያ ፕላት ፎርሞች ተደራሽ የሆኑበት ዉጤታማ ስራዎች መሰራታቸዉን ጠቁመዋል፡፡
ሴክተሮች የማህበራዊ ፕላት ፎርሞችን አማራጭ በማስፋትና በመጠቀም ወቅታዊ መረጃዎችን ለማህበረሰባችን በማድረስ ፤ልምድና ተሞክሮን በማስፋት፤ተቋማት የመረጃ ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግና ወደ ተቀራረበ አፈፃፀም ማምጣት ፤የክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ስልጠናዎችን ማጠናከር እና የበጀት፤ የሰዉ ሃይል እና የግብዓት ችግሮችን መፍታት በቀጣይ ጊዜያት ሊተኮርባቸዉ የሚገቡ የቀጣይ አቅጣጫዎች ናቸዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በየደረጃዉ የሚገኙ የኮሚኒኬሽን መዋቅር አባላት ሙያዊ ብቃትን በመሰነቅ በከተማዋ ሁለተናዊ አጀንዳዎች ላይ ግንዛቤ በመፍጠር በሙሉ ኃላፊነትና ቁርጠኝነት ተልኳቸዉን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ያሉት የቢሮዉ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘዉዱ ከበደ ይህም የሚረጋገጠዉ ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት ተደራሽ የማድረግና የህዝብ እርካታን ማረጋገጥ ሲቻል ነዉ ብለዋል፡፡
አክለዉም ሁሉም ሴክተር በተሰጠዉ ስራ ላይ በሚያስመዘግበዉ ዉጤት መለካት እንዳለበት ገልፀዉ ለተሻለ አፈፃፀም እንደ እነዚህ ያሉ መድረኮችን እና የድጋፍና ክትትል አግባቦችን የበለጠ በማጠናከር ችግሮችን በጋራ መፍታት እንደሚጠበቅ ጠቁመዉ ለዚህም ቢሮዉ አሁንም የበኩሉን ሚና እንደሚወጣና ሁሉም ሴክተሮች የመረጃ ተደራሽነትን ፍጥነትና ብቃት በተሞላበት ወቅታዊ መረጃን የማዳረስና በሁሉም ረገድ በቂ ግንዛቤ የሚገኝበት የመረጃ ምንጭ በመሆን ማህበረሰባችን በቂ ና ሁለንተናዊ መረጃ እንዲኖረው መሰራት ይጠበቃል ብለዋል። በቀጣይም በትኩረት ና በጥምረት መስራት የሚገባቸውን ተግባራት በማስቀመጥ ውይይቱን አጠናቀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.