“ይህ ዘመን በታሪካችን በጉልህ የሚወሳ አዲስ ም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

“ይህ ዘመን በታሪካችን በጉልህ የሚወሳ አዲስ ምእራፍ ነው” ክቡር ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክቡር ታዬ አጽቀስላሴ በህዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህ ዘመን በታሪካችን በጉልህ የሚወሳ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ክቡር ፕሬዚዳንቱ በአዲሱ አመት መባቻ የአመታት ቁጭታችንን እና የጥረታችንን ውጤት የሆነውን ታላቁን የህዳሴ ግድብ ያስመረቅንበት እና የተፈጥሮ ጋዝ ያወጣንበት እንዲሁም ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የጀመርንበት በመሆኑ ይህ ዘመን በታሪካችን ውስጥ በጉልህ የሚወሳ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

መንግስት የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ በትምህርት ጥራት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ትምህርት ለትውልድ በሚል ንቅናቄ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

በጤናው ዘርፍ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት በህክምና ተቋማት ላይ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸው፣ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን በሃገር ውስጥ በማምረት በጤና ተቋማት የሚስተዋለውን የህክምና መሳሪያ ችግር ለመቅረፍ መሰራቱንም አንስተዋል፡፡

በተለይም በህጻናት እድገት  እና በትምህርት ላይ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት ክቡር አቶ ታዬ፣ ሴቶች እና ወጣቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት ውሳኔ ሰጪነታቸው እንዲጨምር  ከተሰሩ ስራዎችም ባሻገር በወጣቶች እና በአካል ጉዳተኞች ተጠቃሚነት ላይ የሚታዩ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

ሃገራችን ጠንካራ አቅም ገንብታለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ አለመግባባትን በመግባባት በመቀየር እና የመፈጸም አቅማችንን አጉልተን በማውጣት ታላቁን የህዳሴ ግድብን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቃችን  እንዲሁም በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር  የተመዘገቡ ውጤቶች በጉልህ የሚጠቀሱ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የተፈጥሮ ጋዝ ልማት እና ግዙፍ የማዳበሪያ ማምረቻ ተቋም መገንባት መጀመሩን አንስተው፣  እነዚህን አጠናቀን ተግባራዊ ስናደርግ የሃገራችን ብልጽግናና ዕድገት የሚታይና የሚዳሰስ እውነት መሆኑ አይቀሬ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.