የወጣቶችን ክህሎት በማጎልበት የውጪ እና የሃገር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የወጣቶችን ክህሎት በማጎልበት የውጪ እና የሃገር ውስጥ የስራ እድሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ስለመቻሉ ተገለፀ

የወጣቶችን ክህሎት በማጎልበት የውጪ እና የሃገር ውስጥ የስራ እድሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ስለመቻሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የስራ ዘመን የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ በርካታ ማህበራዊ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

መንግስት በሚያከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ዋና መገለጫው አካታችነት መሆኑን የገለፁት ኘሬዚዳንቱ፤ ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ በመደረጋቸው ተሣትፏቸውንና ሁለንተናዊ አቅማቸውን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

መንግስት ለአረጋውያንና ሴቶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመስራቱ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል ።

መንግስት ለመጪው ትውልድ ሰፊ ትኩረት የሚሰጥ መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ በህፃናት እድገት እና ትምህርት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ 

የወጣቶችን ክህሎት በማጎልበት የውጪ እና የሃገር ውስጥ የስራ እድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ አእምሮአዊ እና አካላዊ እድገትን ለማዳበር የሚያስችሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት መገንባታቸውንም አክለዋል።

የነገዋ ሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ፣ዘመናዊ የአይነ-ስውራን ትምህርት ቤት ግንባታን፣ የዘመነ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፉ ዲጅታላይዜሽን ስራዎች መከናወናቸውን ነው ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የገለፁት ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.