
በአዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉራዊ ኩነቶች ፣ የአደባባይ ክብረ በአሎች በተከታታይ ከፍ ባለ ስነ-ስርአት ፣ ደማቅ ፣ ዉብ ፣ ፍፁም ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆነዉ መከናወናቸዉ የከተማዋን የትኛዉንም ኩነት በብቃት የማስተናገድ ችሎታዋ እያደገ መምጣቱን ያሳያል
አዲስ አበባ የአደባባይ በአሎችንና ትላልቅ ኩነቶችን የማስተናገድ አቅሟ እያደገ የመጣ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑን የከተማዉ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ገምግሟል ፣
ለአብነትም በከተማዋ የተካሄዱት የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ፣ የአፍሪካ ካረቢያን መሪዎች ጉባኤ፣ የህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ህዝባዊ ሰልፍ ፣ የመስቀል ደመራ ፣ ኢሬቻን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጥቶ ያለ አንዳች ኮሽታ ፣ አንድም መሰረተ ልማት ሳይበላሽ ፣ በታላቅ ስነስርአት ፣ ደማቅና ዉብ ሆነዉ እንዲስተናገዱ ማስቻል ትልቅ ትርጉም የሚሰጠዉ ነው ።
ለዚህም በከተማዉ የተሰሩ የልማት ስራዎችና መሰረተ ልማቶች ወደ አደባባይ ለሚተመዉ ነዋሪና ጎብኚ የሚፈጥሩት ተጨማሪ ዉበት እና ምቾት አዲስ አበባን የስህበት ማዕከል ማድረጉን የተገመገመ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ ኢኮኖሚዉን ያነቃቃና የአለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም አንስቷል ።
በዋናነት የከተማው ህዝብ በሀላፊነት ስሜት ፣ በሃይማኖት ፣ በብሄር ፣ በፓለቲካ አቋም ሳይለያይ ፣በወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስ ከመንግስት ጋር በሁሉም መስክ መስራቱ ፣ የሆቴልና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣ በከፍተኛ ዝግጅት አገልግሎት ማቅረባቸዉ ፣ እንዲሁም ምርቶቻቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ገበያ በማቅረብ የምርት እጥረት እና የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ የግብርና ምርት አቅራቢዎች ፣ የፓለቲካ አመራሩ እና የፀጥታ ተቋማት በቅንጅት የተሰራ ስራ ዉጤት ስለሆነ ለሁሉም አካላት ከልብ ምስጋና ይገባቸዋል ።
በመተባበርና በመደጋገፍ የተመዘገበው ስኬት ለኢትዮዽያ ትልቅ የአብሮነትና የማንሰራራት መሰረት ስለሆነ ይበልጡን አጠናክረን እናስቀጥላለን ብሏል የከተማው ከፍተኛ አመራር።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.