
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በደማቅ ና ባማረ መልኩ መጠናቀቁን የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ በማለት በመግለጫቸው ገለፁ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች ለሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ታዳሚዎች ላደረጉት የሞቀ ቤተሰባዊ አቀባበል ምስጋና ይገባቸዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ለማክበር ለመጡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች የሞቀ አቀባበል በማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ ገለጹ፡፡
የቱለማ አባ ገዳ ጎበና ሆላ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደውን የ2018 ዓ.ም ሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል መጠናቀቁን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
አባ ገዳ ጎበና በመግለጫቸው፣ ሁሉም ብሔሮች ብሔረሰቦች በጉጉት የሚጠብቁት ኢሬቻ በሆረ ፊንፊኔ በድምቀት ተከብሯል ብለዋል።
ኢሬቻ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ቋንቋና ባህል በድምቀት ያከበሩት መሆኑን ገልጸው፤ በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ መከናወኑን ገልጸዋል፡፡
የአንድነት፣ የመተባበርና የሰላም መገለጫ በመሆነው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ላይ ከኢትዮጵያውያን አልፎ በርካታ የውጭ ዜጎች መሳተፋቸውንም ተናግረዋል፡፡
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ ኢትዮጵያውያን ወንድማማችና የጋራ እሴት ያለን መሆኑን ያሳየንበት በዓል ነው ብለዋል፡፡
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የአንድነት የጥንካሬና የመከባበር እሴት ማሳያ ሆኖ በድምቀት መከበሩን ገልጸዋል፡፡
ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባና ኦሮሚያ የጸጥታ ሀይሎች ብርድና ጸሀይ ሳይገድባቸው ሚናቸውን ተወጥተዋል ብለዋል።
ወደ ከተማዋ የመጡ የተለያዩ እንግዶችን የትራንስፖርት ችግር እንዳይገጥማቸው አውቶቡስ በማሰማራት አብሮነቱን ማሳየቱን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ የጤና ሚኒስቴር፣ እና የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮዎች ሊከሰቱ ለሚችሉ የጤና እክሎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስምሪት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በአምስቱም የመግቢያ በሮች ለኢሬቻ ተሳታፊዎች ላደረጉት የሞቀ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በአጠቃላይ በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ የፌዴራል፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና ኦሮሚያ ክልል መንግስት የከበረ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.