.png)
የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ አከባበር ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እጅግ በደመቀና ባማረ ሁኔታ ተጠናቅቋል ።
የሆረ ፊንፊኔ እሬቻ ክብረ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች፣ የተለያዩ አገራት ጎብኚዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች በታደሙበት በልዩ ሁኔታ ደምቆ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቅቋል ።
በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻዎች ልማት ያማረችዉ አዲስ አበባችን ለአደባባይ ክብረ በዓላት፣ ለበዓሉ ታዳሚያንና ከመላዉ ዓለም ለሚመጡ ቱሪስቶች ተጨማሪ ድምቀት እና ምቾት ሆናለች ።
በዓሉ እጅግ ባማረ፣ ደማቅና ሰላማዊ በሆነ መልኩ እሴቱንና ቱፊቱን ጠብቆ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ፣ በተለይም ለከተማችን ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ።
ፈጣሪ ኢትዮዽያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.